የካውንስሉ ሥራ አስፈጻሚ አባላት የሥራ ሃላፊነት

ጸደቀ ይሁኔ ወልዱ

ሰብሳቢ

ኢንጅነር. ጸደቀ ይሁኔ ወልዱ

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻሻያ ካወንስል ሊቀመንበር እና የፍሊንት ስቶን ቤቶች ኢንጅነሪንግ መስራች፡፡

ደንጌ ቦሩ

ምክትል ሰብሳቢ

ክቡር አቶ. ደንጌ ቦሩ

ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ

ሚኒስቴር ደኤታ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ኤልሳቤጥ ጌታሁን

ጸሀፊ

ወ/ሮ. ኤልሳቤጥ ጌታሁን

ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ጌታሁን የፓናፍሪክ ግሎባል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሆኑ፤ የሚመሩት ኩባንያ በኢትዮጵያ  የሎጂስቲክስ ዘርፍ ቀዳሚ ድርሻ ካላቸው የግል ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ የአገሪቱ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ዘመናዊ እንዲሆንና ተገቢውን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ከተቋቋሙት አገር አቀፍ ማህበራት አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (EFFSAA) በቦርድ አባልነትና አሁን ደግሞ የማህበሩ ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት የኢትዮጵያ ሎጅስቲክስ  ማህበረሰብንም (ELCoP) እውን ለማድረግ ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከምስረታው ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ ባለሙያ ናቸው ፡፡

በሎጅስቲክስና ትራንስፖርት ዘርፍ ከሃያአምስት ዓመታት በላይ የሙያ ልምድ ያላቸው ሲሆን፤ በዘርፉ የፖሊሲ መሻሻል እንዲኖር፣ አዳዲስና ዘመናዊ አሰራሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም ለዘላቂ የጭነት ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ሽግግር ለውጦች አስተዋፅዖ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ዘርፉን ለማሻሻል በሚያስችሉ በርካታ መድረኮች እና የፓናል ውይይቶች ላይ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ዋና ተናጋሪ በመሆን ታላቅ ድርሻ አላቸው፡፡

ሙላት ለምለምአየሁ

አባል

ካፒቴን. ሙላት ለምለምአየሁ

ካፒቴን ሙላት ለምለምአየሁ በአገሪቱ ውስጥ ካሉት የግል በረራ ድርጅቶች አንዱ የኢስት አፍሪካን አቪዬሽን ባለቤት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ በበረራ አገልግሎት ላይ በሚሰሩበት ጊዜም በአመታት ውስጥ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በርካታ የቻርተር መንገደኞችንና በደርዘን የሚቆጠሩ ታካሚዎችን በማገልገል ሰርተዋል፡፡ እንዲሁም የአየር መንገድ የአምቡላንስ አገልግሎትም ሰጥተዋል፡፡ በአቪዬሽኑ ውስጥ በነበሩበት ጊዜም ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው አገልግሎቶች እንዲሰጡ የበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ የኢስት አፍሪካ አቪዬሽንን ከመመሥረታቸው በፊት ካፒቴን ሙላት የንግድ ሥራ ጀት አብራሪ ሆነው ለ39 ዓመት ያገለገሉ ሲሆን ዲሲ- 3 ቢ -727 ቢ -767 ቢ- 777 እና ቢ -787 የተባሉ ዘመናዊ ጀቶችንም አብርረዋል፡፡

 

 

ከአቪዬሽኑ ዘርፍ በተጨማሪም የባለ 4 ኮከብ ሆቴል እና የበርካታ ከፍተኛ ምግብ ቤቶች ባለቤት ናቸው ፡፡ በአቪዬሽኑ ዘርፍ ያካበቱት የሥራ ልምድ እና አስተዋጽኦ እንዲሁም ያላቸው የማኔጅመንት ብቃት ለትራንስፖርት ዘርፋ መጐልበት ጠቃሚ ሚና ተጫውቷል፡፡

እንግዳዬ እሸቴ

አባል

ወ/ሮ. እንግዳዬ እሸቴ

ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ የኢጋድ ኘሬዚዳንት እና የሴት ነጋዴዎች ፎረም ምክትል ኘሬዚዳንት ናቸው፡፡ እንደ ኢንተርፐርነር በሾኔ ከተማ የሚገኘው የእናት ዓለም ሆቴል ባለቤት እና አስተዳዳሪ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የሆቴሉ ሙሉ ሥራ በሴት ልጆቻቸው የሚሸፈን ሲሆን እሣቸው በበላይነት እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ፡፡ወ/ሮ እንግዳዬ በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች በነበሩበት ጊዜ ለሴት ነጋዴዎች ማህበር መመሥረት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተለይም በ2010 ዓ.ም ለማህበሩ በክልሉ መመስረት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የማህበሩ ኘሬዝዳንት በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

--

አባል

--. --

--

አንዱአለም ሙሉጌታ

አባል

አቶ. አንዱአለም ሙሉጌታ

ብርሀኔ ዘርኡ

አባል

አቶ. ብርሀኔ ዘርኡ

አባይነህ ጉጆ

አባል

አቶ. አባይነህ ጉጆ

አቶ አባይነህ ጉጆ ከ2ዐዐ5 ዓ ም ጀምሮ  FENAPD ተብሎ በሚጠራ ድርጅት ውስጥ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ ከዚያ በፊትም በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ የተለያዩ ሃላፊነቶችን በመውሰድ በብቃት የተወጡ ናቸው ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከ1997 እስከ 1999 ዓ .ም. ድረስ በጣሊያን ሴንተር ፎር ችልድረን ኤድ (Center for children Aid)፤ ከ1999ዓ .ም. እስከ 2ዐዐ3 ዓ .ም ድረስ ሊንከ ኮሚዩኒቲ ዴቨሎኘመንት ሴንተር( link communite development center)  እና ከ2ዐዐ3 ዓ ም እስከ 2ዐዐ5 ዓ ም ዲ ፎር ዲ (D for D) በሚባል ድርጅት ውስጥ በማኔጅንግ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡በአሁኑ ወቅትም አቶ አባይነህ በኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር በሚገኘው የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንሥል ውስጥ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ ፡፡

አሰፋ ሃዲስ

በካውንሥሉ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተጠሪ

አቶ. አሰፋ ሃዲስ

አቶ አሰፋ ሃዲስ የኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ምክትል ዋና ጸሀፊ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን ፡፡ ላለፉት 14 ዓመታት  በገጠር ልማት ስራዎች በተለይም የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ እና የእጽዋት እና የአዝመራ ባለሙያ በመሆን ሲያገለግሉ የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ አንጻር  የደን መጨፍጨፍን ለመቀነስ የበኩላቸውን አስተዋጾ አበርክተዋል፡፡ በተጨማሪም አቶ አሰፋ የመረጃ ተንታኝ ፤ገምጋሚ እንዲሁም የማሻሻያ ትግበራ እና የግምገማ ባለሙያ ዋና ሂደት አስተባባሪ በመሆን ሰፊ የስራ ልምድ አካብተወዋል፡፡