የካውንስሉ የድረ ገጽ ፖሊሲ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል የተጠቃሚው ህብረተሰብ አይንና ጆሮ በመሆን በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ተገልጋዩ ህብረተሰብ ያለውን አስተያየት እና ቅሬታ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ማምጣት በሚችል መልኩ የአሰራር ስርአት መዘርጋት እንዳለበት ያምናል፡፡ አገልግሎቶችን በተመለከተ በሂስ ሰጭው የሚሰጠው ቅሬታ፣አስተያየት እና መረጃ ካውንሥሉ አገልግሎቱ ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት በአግባቡ የሚጠቀምበት ሲሆን በመረጃ አጠቃቀም ሂደቱም ከካውንሥሉ ውጭ ላለ ለሌላ አካል የማይሰጥ መሆኑን ካውንስሉ ማረጋገጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የሂስ ሰጪውን ማንነት የሚገልጹ እንደ ስም፣ የስልክ አድራሻ፣ የሥራ ወይም የመኖሪያ ቦታ አድራሻዎች ግልጽ የማይደረጉ ሲሆን ቅሬታውን ለመፍታት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ሂስ ሰጭው በካውንስሉ አባላት ጋር የሚገናኝበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ካውንስሉ ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል፡፡
በሌላ በኩል ግን እነዚህ መረጃዎች በካውንስሉ ቢሮ በኩል የሚፈለጉ ሲሆን የአስተያየት ሰጭውን ማንነት ወይም በአስተያየት ሰጭው በኩል የተሰጠውን አስተያየት ተአማኒነት ለመመዘን ቢሮው የሚጠቀምበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በተጨማሪም በድረ ገጹ ላይ የሚሰጠው አስተያየት ተገቢነቱን ለማረጋገጥ በጽሁፍ መልክ የሚመጡ አስተያየቶችን እስከ 6 ሰዓትና በኦዲዩ ቪዠዋል መልክ የሚላኩ መልእክቶችን እስከ 24 ሰዓት ድረስ የምናቆይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመሆኑም ይህንን በመገንዘብ አስተያየት ሰጭዎች ድረ ገጹን በሃላፊነት እንዲጠቀሙበት ለማድረግ አስተያየት ሰጭውን ሙሉ አድራሻ በድህረ- ገጽ አስተያየት መስጫ ቅጽ ላይ እንድትመዘግቡ እየጠየቅን ሆኖም ግን ይህ ግዴታ እንዳልሆነ ማሳወቅ እንወዳለን፡፡