የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል ህዳር 3 ቀን 2013 አ.ም ከአባላት ጋር ያከናወነው ጠቅላላ ጉባኤ።

የኢፌድሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል ህዳር 3 ቀን 2013 ዐ.ም ከአባላት ጋር ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ያከናወነውን የስራ ሪፖርት አቅርቧል፤ ያቀረበው የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ላይ አባላት ያላቸውን ሃሳብ እና አስተያየት በግብአትነት ተቀብሎ መተዳዳሪያ ደንቡን አጽድቋል፤የፋይናንስ አቅሙን በተመለከተ ከአባላት ጋር መክሮ አቅጣጫ ይዟል፤አባላት በድህረ ኮሚቴ ተሳታፊ የሚሆኑበትን አደረጃጀት አቅርቦ ፍቃደኛ የሆኑ አባላትን መዝግቧል፤ አባላት ካውንስሉ እንዲሰራላቸው ሚፈልጉትን ጉዳዮች እና አካሄዶች በመመካካር ተሳታፊ የሚሆኑበትን አሰራር ላይ ተወያይቶ የእለቱን የምክክር ጉባኤ አጠናቋል፡፡