የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ አመት ሪፖርት በየካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም አቅርቧል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ አመት ሪፖርት በየካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና የካውንስሉ አባላት በተገኙበት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቧል፡፡

በሪፖርቱ አገልግሎት አሰጣጦችን የተመለከቱ ጥናቶች የአውቶቡስ ተራ፣ ኮተቤ ላም በረት እና አየር ጤና መናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የሚቆጣጠራቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ፣ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ እና በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተከናወነ ጥናት በካውንስሉ ቀርቧል፡፡

ከነዚህም በተጨማሪ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የልምድ ልውውጦች የክትትል እና ድጋፍ ስራዎች እና ከባለድርሻ አካላት ለካውንስሉ የተሰጡ ምላሾች ሪፖርት ቀርቧል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በኩልም የስድስት ወራት የስራ ክንውኖች የቀረቡ ሲሆን ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዙሪያ አለም አቀፋዊ ቀጠናዊ ግንኙነቶች፣ የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በተመለከተ፣ የህግ ማእቀፎች እና የውስጥ አሰራር ማሻሻያ ስራዎች በተለያየ ዘርፎች ላይ የተተገበሩበት አግባብ ባቀረቡት ሪፖርት ተዳሷል፡፡

አዳዲስ ዜናዎች የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ አመት ሪፖርት በየካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም አቅርቧል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ አመት ሪፖርት በየካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም አቅርቧል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም የበጀት አመቱን የሩብ አመት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል በጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ከአባላቶቹ ጋር አከናውኗል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ካውንስሉ ያደረጉት ጉብኝት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሪፖርት በስፋት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የአገልግሎት ማሻሻያ ካውንስሉ የመጨረሻ ሩብ አመት ሪፖርት ካውንስሉ በመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ያከናወነው የስራ ጉብኝት ካውንስሉ በኢባትሎአድ ያከናወነው የስራ ጉብኝት የዘጠኝ ወር ሪፖርት የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካውንስል ህዳር 3 ቀን 2013 አ.ም ከአባላት ጋር ያከናወነው ጠቅላላ ጉባኤ። የካውንስሉ አባላት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጉብኝት ወቅት