
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን በሀገሪቱ ውጤታማ እና አርኪ የማሪታይም ኢንዱስትሪ ለመፍጠር ሃላፊነት ተሰጥቶት እየሰራ ያለ ድርጅት ሲሆን ለህብረተሰቡ የስራ እድል እና የተሻለ የኑሮ ደረጃ በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ ያለው ድርጅት እንዲሆን አትኩሮት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ድርጅት በዋቢነት ወደ ህብረተሰቡ ተደራሸ የሚያደርጋቸው አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡
- አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት እና ማደስ
- ምትክ የብቃት ማረጋገጫ እና የድጋፍ ደብዳቤዎች መስጠት
- አዲስ እና ምትክ የባህረኛ መታወቂያ ደብተር መስጠት እና ማደስ
- የመሰረታዊ የባህር ደህንነት ሰርተፊኬት መስጠት፤ ሲጠፋ ምትክ መስጠት እና ማደስ
- የተለያዩ የምስክር ወረቀቶችን አዲስ እና ምትክ መስጠት፤ ማደስ
- ለተለያዩ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ መስጠት
- የመርከብ ምዝገባ ማካሄድ እና የመርከብ ስም ፍቃድ መስጠት
- የጀልባ ግንባታ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ፍቃድ መስጠት
አስተያየትዎን በማስገባት በድር ጣቢያው መመሪያዎች እንዳነበቡ እና እንደተስማሙ ይገነዘባል ፡፡ እነዚህን መመሪያዎች እዚህ ማንበብ ይችላሉ እዚህ
* ምልክት ያላቸው ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ