_1601552231_1648708988.jpg)
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን
የአገሪቱን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በ1937 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን ፤ እ.ኤ.አ. በ2025 ከአደጋ ሥጋት የፀዳ የአየር ክልል የማስተዳደር ራዕይ ሰንቆ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡ ለዚህም ራዕይ መሳካት ባለሥልጣን ድርጅቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ኅብረተሰቡ እንዲያገኝ አሠራሩን በማዘመን፣ ዘመናዊ የበረራ መቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን ገዝቶ በመግጠምና የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በስፋት በማሠልጠን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በዋናነትም የሚሰጠው አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ለአየር መንገዶችና ተጓዳኝ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት፣
- አየር መንገዶችንና አውሮፕላኖችን በመመርመር የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት መስጠት፣
- ለአብራሪዎች፣ ለቴክኒሺያኖችና ለሌሎች የአቪዬሽን ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ መስጠት፣
- የአውሮፕላን ጥገና ማዕከላትን መፈተሽ፣
- የበረራ ፈቃድና የኤር ናቪጌሽን አገልግሎቶች መስጠት ናቸው፡፡
አስተያየትዎን በማስገባት በድር ጣቢያው መመሪያዎች እንዳነበቡ እና እንደተስማሙ ይገነዘባል ፡፡ እነዚህን መመሪያዎች እዚህ ማንበብ ይችላሉ እዚህ
* ምልክት ያላቸው ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ